ኤርትራ የሚገኙ የሶማሊያ ወታደሮች ወደ ሃገራቸው እንደሚመለሱ ፕሬዚዳንቱ ቃል ገቡ

Your browser doesn’t support HTML5

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼኽ ሞሃሙድ፣ በኤርትራ በመሰልጠን ላይ ያሉ የሶማሊያ ወታደሮች ወደ ሃገራቸው በቅርቡ ይመለሳሉ ሲሉ ከወታደሮቹ ቤተሰቦች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ቃል ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቱ የወታደሮቹን መመለሻ ቀን ባይቆርጡም በቅርቡ ወደሃገራቸው ተመልሰው የእስልምና አክራሪ ከሆነው አል-ሻባብ ቡድን ጋር እንደሚፋለሙ ተናግረዋል።