ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ ገዳይ በሽታዎች በአፍሪካ

Your browser doesn’t support HTML5

በአፍሪካ እየጨመረ የመጣውን እንደ ዝንጀሮ ፈንጣጣ እና ኢቦላ ያሉ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ ገዳይ በሽታዎች መዛመት ለመግታት እርምጃ ይወሰድ ዘንድ የዓለም ጤና ድርጅት ጥሪ አቀረበ።

በአፍሪቃ ከእንስሳት ወደ ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች መጠን ከቀደሙ አስርት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከ2012 እስከ 2022 ዓ/ም ባለው ጊዜ ውስጥ በ63 በመቶ መጨመሩን የዓለም ጤና ድርጅት ይፋ ያደረገው አዲስ የጥናት ዘገባ አመለከተ።

እንደ ዘገባውም በዓለም ዙሪያ የሰውን ልጅ ከሚያጠቁት ተላላፊ በሽታዎች 60 ከመቶው እና አዲስ ከሚከሰቱት ደግሞ ከ75 በመቶው በላይ የሚሆኑት የዱር እና የቤት እንስሳትን በሚያጠቁ በሽታ አምጪ ተህዋሲያን የሚከሰቱ ናቸው።

በእነኚህ በሽታዎች ሳቢያም በዓለም ዙሪያ በየዓመቱ ቁጥሩ አንድ ቢሊዮን የሚጠጋ ሰው ለሕመም ሲጋለጥ ሚልዮኖች ደግሞ ለህልፈት ይዳርጋሉ።