በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩት ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ ዛሬ ፍ/ቤት ቀረቡ

Your browser doesn’t support HTML5

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ትናንት በቁጥጥር ስር የዋሉት አቶ ምትኩ ካሳና ልጃቸው ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ። ሁለቱን ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ያቀረበው የፌደራል ፖሊስ ፣ አቶ ምትኩ ከኤልሻዳይ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመመሳጠር ፈጽመዋል ያሏቸውን የሙስና ወንጀሎች በተመለከተ ያሰባሰበውን ማስረጃ ለችሎቱ አቅርቦ ለተጨማሪ ምርመራ የ14 ቀን ቀጠሮ ጠይቋል፡፡

የፖሊስን የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ በመቃወም መከራከራቸውን ለቪኦኤ የገለጹት የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች፣ ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤት ለፖሊስ የ14 ቀናት የጊዜ መፍቀዱን ተናግረዋል፡፡