ኤፍራታ ግድምና ጅሌ ጥሙጋ እየተረጋጉ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች አጎራባች አካባቢዎች ሰሞኑን በተቀሰቀሰው ግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች እየተመለሱ መሆናቸው ተገልጿል።

ይሁን እንጂ “ሸኔ” ሲሉ የጠሯቸው ታጣቂዎች ሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ጠቅሰው የደኅንነት ሥጋት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፓርላማ በአሸባሪነት የፈረጀውና ባለሥልጣናቱ “ሸኔ” የሚሉት “የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት” እንደሆነ የሚናገረው ቡድን “በሰላማዊ ሰዎች ግድያ ላይ እጁ እንደሌለበት” በዓለምአቀፍ ቃል አቀባዩ መሆናቸው በሚገልፁ ተጠሪው በኩል ሲያስተባብል መቆየቱ ይታወሳል።