የፍትሕ መጽሔት ባለቤትና ማኔጂንግ ኤዲተር ተመስገን ደሳለኝ ዋስትና ታግዷል

Your browser doesn’t support HTML5

ዋስትናው የታገደው፣ በተመስገን ላይ ሦስት የወንጀል ክሶችን የመሰረተው ዐቃቤ ሕግ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ በማቅረቡ መሆኑን ጠበቃው አቶ ሄኖክ አክሊሉ ገልጸዋል።

በሌላ ዜና ለ51 ቀናት በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸውን ፍ/ቤት ሲካታተሉ የነበሩ ስምንት “አሻራ”ና “ንስር” የተባሉ የዩቲዩብ ሚድያ ሰራተኞች በዋስ እንዲለቀቁ በፍርድ ቤት ቢወስንም እስካሁን አለመፈታታቸውን ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል፡፡