ሰዎች ከመኪና እንዲወርዱ ተደርገው በተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ የመንግሥት ኃይሎች ጭምር መሳተፋቸውን ኢሰመኮ ገለፀ
Your browser doesn’t support HTML5
በርካታ ሰዎች ከመኪና እንዲወርዱ ተደርገው በጅምላ ሲገደሉ የሚያሳየው አሰቃቂ የግድያ ድርጊት መደበኛ እና ኢ-መደበኛ የመንግሥት ኃይሎች ከወራት በፊት የፈጸሙት መሆኑን ኢሰመኮ ገለጸ።
ድርጊቱ የተፈጸመው ባለፈው ታኅሳስ ወር መሆኑን ኮሚሽኑ ባደረገው ምርመራ ማረጋገጡን ለአሜሪካ ድምፅ ያብራሩት የሰብዓዊ መብቶች ክትትል ምርመራ ሲኒየር ዳይሬክተር አቶ ይበቃል ግዛው፣ ቪዲዮው ከዚህ በፊት ካለው መረጃ፣ ተጨማሪ ኃይሎች በድርጊቱ ስለመሳተፋቸው እንደሚጠቁም ገልጸዋል፡፡