በርካታ ሰዎች ከመኪና እንዲወርዱ ተደርገው በጅምላ ሲገደሉ የሚያሳየው አሰቃቂ የግድያ ድርጊት መደበኛ እና ኢ-መደበኛ የመንግሥት ኃይሎች ከወራት በፊት የፈጸሙት መሆኑን ኢሰመኮ ገለጸ።
ድርጊቱ የተፈጸመው ባለፈው ታኅሳስ ወር መሆኑን ኮሚሽኑ ባደረገው ምርመራ ማረጋገጡን ለአሜሪካ ድምፅ ያብራሩት የሰብዓዊ መብቶች ክትትል ምርመራ ሲኒየር ዳይሬክተር አቶ ይበቃል ግዛው፣ ቪዲዮው ከዚህ በፊት ካለው መረጃ፣ ተጨማሪ ኃይሎች በድርጊቱ ስለመሳተፋቸው እንደሚጠቁም ገልጸዋል፡፡
ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ባደረገው ምርመራ ጉዳዩን ለመንግሥት በማሳወቅ ተጨማሪ ምርመራ ተደርጎ አጥፊዎች ለሕግ እንዲቀርቡ ማሳሰቡንም አንስተዋል። በኮሚሽኑ የሚሰጡትን ምክረ ሐሳቦች ለመተግበር ጥረቶችን በማድረግ ላይ መሆኑን መንግሥት በተደጋጋሚ ቢያሳውቅም፣ በዚህ ግድያ ዙሪያ ግን በተናጥል ያለው ነገር የለም፡፡
አቶ ይበቃል ግዛው፣ ባለፈው ቅዳሜ ሰኔ 11 በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ የተፈጸመውን ጥቃት በተመለከተ ደግሞ፣ በጥቃቱ በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የሚሰሙ ግድያዎች በማኅበረሰቡ ላይ ያላቸውን ተጽዕኖ በተመለከተ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ አጥኚ አቶ ፍሰሐ ተክሌ አስተያየታቸውን ሰጥተውናል፡፡
Your browser doesn’t support HTML5
/ሙሉ ዘገባውን ከተያይዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ/