ሀገራዊ ቀውሶች እና መፍትሄዎችን ያንጸባርቃሉ የተባሉ የሸክላ ላይ ስዕሎች ለዕይታ ቀረቡ

Your browser doesn’t support HTML5

ባለፈው ቅዳሜ የተከፈተው ዓውደ ርዕዩ እንስራ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በሸክላ ላይ የተሳሉ ስዕሎች ለዕይታ የቀረቡበት ነው፡፡ በአፍሪካ ደረጃም ቢሆን መሰል የሸክላ ላይ ስዕሎች ዓውደ ርዕይ የተለመደ እንዳልሆነ የሚገልጸው ሰዓሊው፣ በሸክላ ላይ የጥበብ ስራዎቹ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለውን ሀገራዊ ቀውስ በማንጸባረቅ እያንዳንዱ ሰው ለመፍትሔው ምን ማበርከት እንደሚችል ማመልከት ዓላማው መሆኑን ይገልጻል፡፡