የአሜሪካዎቹ ጉባዔ፣ ብሊንከንና የፕሬስ ነፃነት

Your browser doesn’t support HTML5

“ዩናይትድ ስቴትስ ‘የፕሬስ ነፃነትን አደጋ ላይ ጥለዋል’ የምትላቸውን እንደ ኪዩባ፣ ኒካራጓና ቬንዝዌላ የመሳሰሉ አገሮችን እያወገዘች እንዴት ጋዜጠኛ በመግደል ጭምር ከሚወነጀሉት እንደ ሳዑዲ አረቢያ ካሉ አገሮች ጋር ትሠራለች?” የሚል ጥያቄ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ቀርቦላቸዋል።

ካሊፎርኒያዋ ሎስ አንጀለስ ውስጥ ከሚካሄደው የደቡብና የሰሜን አሜሪካ አገሮች ዓለምአቀፍ ጉባኤ ጎን ለጎን የጋዜጠኛነት ትምህርት በመከታተል ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች ንግግር ባሰሙት ወቅት ነው የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲህ ዓይነትና ሌሎችም ጥያቄዎች የተሠነዘሩላቸው።

የዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ከፍተኛ ሪፖርተራችን ሲንዲ ሴይን ያጠናቀረችውን ዘገባ ዝርዝር አሉላ ከበደ ወደ አማርኛ መልሶታል።