“ኢትዮጵያ ክስ ያልቀረበባቸውን ጋዜጠኞችን እስር ላይ እያቆየች ነው”
Your browser doesn’t support HTML5
በኢትዮጵያ ፖሊስ ባለፈው ወር በቁጥጥር ስር ያዋላቸውን ቁጥራቸው 19 የሚደርሱ ጋዜጠኞች እስካሁን ክስ ሳይመሰረትባቸው እስር ቤቶች ይዞ እንዳቆያቸው ተዘገበ። የመብት ተሟጋች ድርጅቶች መንግስት በትግራይ በሚካሄደው ጦርነት እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ በሚያቀርቧቸው ዘገባዎች ራሳቸውን ሳንሱር እንዲያደርጉ ለማስገደድ ሆን ብሎ በጋዜጠኞች ላይ ያነጣጠረው እርምጃ ነው ሲሉ ይወቅሳሉ።
ሃሊማ አቱማኒ ከአዲስ አበባ ያጠናቀረችውን ዘገባ ዝርዝር ከዚህ ያድምጡ።