በአስር ወራት ውስጥ 1.3 ሚሊዮን ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸውን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

በ2014 ዓ.ም የመጀመሪያ አስር ወራት ውስጥ ብቻ ኢትዮጵያ ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በወባ በሽታ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። የጤና ሚኒስቴር ዛሬ ወቅታዊ የጤና ሁኔታዎችን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ላይ የተናገሩት ሚኒሰትር ዲኤታው ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ በተለያዩ የአለም ሀገራት የተከሰተው የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ እስካሁን በኢትዮጵያ አለመከሰቱን ገልጸዋል ። ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ግን ዳግም እያንሰራራ መሆኑን አመልክተዋል።