ከቀርቅሀ ለአካል ጉዳተኞች አጋዥ መላን ስለፈጠረው ወጣት በጥቂቱ

Your browser doesn’t support HTML5

ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ተፈጥራዊ እና ሰው ሰራስ ምክንያቶች ለመንቀሳቀስ ያልቻሉ ወገኖች ከሚቸገሩበት ጉዳይ መካከል አንዱ ለመንቀሳቀሻ የሚሆን ተሽከርካሪ ወንበር አለማግኘት ነው። ይሄንን ችግር የተመለከተ አንድ ወጣት በሀገር በቀል አማራጮች ችግሩን ለመቅረፍ ጥረቱን ከጀመረ ሰነባብቷል። አቤል ኃ/ጊዮርጊስ ይባላል ።ከቀርቀሃ የተለያዩ ቁሳቁሶችን የሚገነባ "ባምቡ ላብ" ድርጅት መስራች ነው። ለአካል ጉዳተኞች የሚሆኑ ተሸክርካሪዎች እና ብስክሌቶችን ከቀርቅሃ በማምረት ትኩረት እያሰበ ከሚገኘውን አቤል ኃ/ጊዮርጊስ ጋር ቆይታ ያደርገው ሀብታሙ ስዩም ነው። አቤል ስለ ስራው አጃማመር ቀድሞ ያስረዳል ።