በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች “አፍሪካን አርሚዎርም” የተሰኘ ተምች ወረርሽኝ 10 ሺሕ ሄክታር መሬት መውረሩን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
የክልሉ አርሶ አደሮችም ተምቹ በበቆሎ፣ በሩዝ በጤፍ እና በዳጉሳ ቋሚ ሰብሎች ላይ ጉዳት ማድረሱን ገልፀዋል።
የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል እና የእርሻ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ክንፉ በክልሉ አራት ዞኖች እና 12 ወረዳዎች መከሰቱን ተናግረዋል።