ቆይታ ከወጣቷ የስነ ጥበብ ባለሙያ ኑር አንዋር ጋር

Your browser doesn’t support HTML5

ኑር አንዋር ትባላለች የ20 ዓመት ወጣት ነች። ከልጅነቷ ጀምሮ ባዳበረችው የስዕል ተሰጥዖ አለም አቀፍ የታዳጊዎችን ውድድር እስከማሸነፍ ደርሳለች። በቅርቡም በድሬዳዋ አሊያንስ ኢትዮፍራንሴ የመጀመሪያዋን የስዕል ኤግዚቢሽን አዘጋጅታለች። የስዕል ፍቅሯ ከትምህርቷ ጋር እንዳልተጋጨባት የምትናገረው ኑር በ12ኛ ክፍል ውጤቷ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ውጤት አምጥታ በሰሞኑ ምደባ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተመድባለች። ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም ስዕሎቿን የምትሸጥ ስትሆን ስዕሎቿ በዋናነት የሚያተኩሩት ተፈጥሮ ላይ እንደሆነ ትናገራለች። ረቂቅ ወይም አብስትራክት ስዕሎችንም ትስላለች። አዲስ ቸኮል በቅርቡ አነጋግሯት ነበር።