ቆይታ ከወጣቱ ኤሌክትሮኒክ የደህንነት ስርዓት ገንቢ ብሩክ ግርማ ጋር

Your browser doesn’t support HTML5

ብሩክ ግርማ ዝንባሌውን በልምምድ እና በተጓዳኝ ትምህርት አሳድጎ በዓመታት ውስጥ የተሳካ የኤሌክትሮኒክስ እና የደህንነት መጠበቂያ ስርዓት አምራች ድርጅት መገንባት የቻለ ወጣት ነው። አራት ያህል የፈጠራ ስራዎቹን በኢትዮጵያ የአዕምሮ ንብረት ጽ/ቤት ለማስመዝገብ የቻለው ብሩክ፣ ፈጠራዎቹ ለህዝብ ጥቅም ይውሉ ዘንድ በተለያዩ ጊዜዎች ፈቅዷል።ሀብታሙ ስዩም ከብሩክ ግርማ ጋር አጠር ያለ ቆይታ አድርጓል።ብሩክ በተለይ የደህንነት መጠበቂያ ስርዓት እንዲፈጥር መነሻ የሆነውን የግል አጋጣሚ በማስረዳት ይጀምራል።