ባይደን የስዊድንና የፊንላንድን የኔቶ አባልነት ጥያቄ ይደግፋሉ
Your browser doesn’t support HTML5
ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ትናንት ሀሙስ ስዊድንና ፊንላንድ ኔቶን ለመቀላቀል ያቀረቡትን ጥያቄ ላቀ ባለ የደስታ ስሜት ተቀብለውታል፡፡ ዘመናዊ ጦር ያላቸው ሁለቱ የአውሮፓ አገሮች፣ ፊንላንድና ስዊድን፣ የኔቶ የደህንነት ህብረትን፣ ወደ ሰሜን ምዕራብ የሩሲያ ድንበር ለማስፋት እንደሚረዱት ተነገሯል፡፡