የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እ.አ.አ የቀን አቆጣጠር በ1973 ዓ.ም የፅንስ ማቋረጥ ህጋዊ እንዲሆን የተላለፈውን ውሳኔ የሚቀለብሰው ከሆነ የአሜሪካ ሴቶች ፅንስ የማቋረጥ መብታቸውን የሚገድብ ይሆናል።
“በሮይ እና ዌድ መካከል ተደርጎ የነበረውን ክርክር ተንተርሶ የተሰጠው ውሳኔ ከተቀለበሰ በዓለም ዙሪያ ምን አይነት ተፅእኖ ይፈጥራል?” ስትል የአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢያችን ቬሮኒካ ባልደራስ ኢግሊሲያስ በሦስት የተለያዩ አህጉሮች ላይ የሚገኙ የለውጥ አቀንቃኞችን አነጋግራለች። እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል።