እቴጌ፦ለኢትዮጵያ ሴቶች መላ የሚያቀብለው መተግበሪያ

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ ሴቶች የጤና ፈተና ከሆኑት መካከል የጡት እና የማሕጸን ጫፍ ካንሰር በሽታዎች ይጠቀሳሉ። በበሽታዎቹ ዙሪያ ያለው የግንዛቤ እጥረት ሴቶች ሳይረፍድ ምልክቶችን ተመልክተው መፍትሄ እንዳያፈልጉ ከልክሏቸዋል። መላ ለማበጀት በበኩላቸው ከሚንቀሳቀሱ ወጣቶች አንዷ ዶ/ር ቤቴል ሳምሶን ናት ። "እቴጌ " የተሰኘ መተግበሪያ ከአጋሮቿ ጋር በማዘጋጀት -ተጠቃሚዎች የመጀመሪያ ደረጃ የበሽታ ምልክቶችን እንዲያውቁ አስችላለች። ተያያዥ ሀሳቦችን ለሀብታሙ ስዩም አጋርተዋለች።