የትውልደ-ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ ለጦርነት ተጎጂዎች

Your browser doesn’t support HTML5

ከሰሞኑ በዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢዎ የሚኖሩ ትውልደ - ኢትዮጵያዊያን ፣ በትውልድ ሀገራቸው በተካሄደው ጦርነት ወቅት የወደሙ ተቋማትን ለመርዳት የሚውል ገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አድርገዋል። በቨርጂኒያ ወተርፎርድ አዳራሽ በነበረው ዝግጅት ላይ ከኪነጥበብ ዝግጅቶች ጎን ለጎን ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የአቅማቸውን ገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ የሚያበረታቱ መርሀ ግብሮች ተከውነዋል። ሀብታሙ ስዩም በዝግጅቱ ላይ ተገኝቶ ከአስተባባሪዎች ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል ።