ልዩ ፍላጎት ላላቸው ህፃናት የሚሰጥ የኮዲንግ ሥልጠና
Your browser doesn’t support HTML5
በኢትዮጵያ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ህፃናት ከሌሎች ተማሪዎች ጋር ተቀላቅለው ለመማር የሚያስችላቸው በቂ ድጋፍ ባለመኖሩ የትምሕርት ተሳትፏቸው በጣም ዝቅተኛ ነው። ራዕይ የተሰኘ አንድ የህፃናት መርጃ ድርጅት ግን እነዚህ ህፃናት ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርቶች ልዩ ተሰጥኦ እንዳላቸው በመረዳት በተለይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላላቸው ህፃናት ነፃ የሞያና የቴክኖሎጂ ስልጠናዎችን በመስጠት ተማሪዎቹ እራሳቸውን እንዲችሉ እያገዘ ይገኛል።ሙሉ ዝግጅቱን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ/