ስድስት የአፍሪካ ሀገራትን ከረሀብ ለመታደግ ተ.መ.ድ 100 ሚሊየን ዶላር ሰጠ

ፎቶ ፋይል - በጦርነት በተመታችው የመን ውስጥ ሆዴዳ ግዛት በሚገኝ ክንሊክ ውስጥ የተመጣጠነ ምግብ እረት ያለባት ልጇን በመመገብ ላይ ያለች እናት። እ.አ.አ . 7, 2021.

በደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ናይጄሪይ፣ ኬንያ እና ኢትዮጵያ ለረሃብ የተጋለጡ በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎችንለመርዳት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከማዕከላዊ የአስቸኳይ ግዜ ምላሽ ፈንዱ100 ሚሊየን ዶላር ማውጣቱንአስታወቀ።

በሰባቱ የአፍሪካ ሀገራት በሚካሄዱ የትጥቅ ትግሎች፣ ድርቅ እና ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ባባሰው የኢኮኖሚ መዋዠቅምክንያት በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች እራሳቸውን መመገብ አልቻሉም ያለው የመንግስታቱ ድርጅት በዩክሬን እየተካሄደያለው ጦርነት ተፅእኖም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለረሃብ እንዳጋለጠ ገልጿል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) ቃል አቀባይ ጄንስ ሌያርክ ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩበተለይ የመን፣ ደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ፣ ተቋሙ አምስተኛ ድረጃ ላይ ያስቀመጠው የድርቅ መቅሰፍት ወይም የረሃብሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ አስረድተዋል።

"ሌሎች ሀገራትም፣ ለምሳሌ ናይጄሪያ፣ ሱዳን እና ኬንያ - ኢትዮጵያን ጨምሮ - በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች የድርቅመቅሰፍት ደረጃ ለመድረስ ቋፍ ላይ ናቸው። እዛ ውስጥ እንዳይገቡ ማድረግ አለብን። አለበለዚያ አይናችን እያየ ሰዎችበረብና በበሽታ ይሞታሉ። ያ እንዳይሆን አሁን እርማጃ መውሰድ አለብን።"

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰባቱን ሀገራት ለመርዳት 43 ቢሊየን ዶላር እንደሚያስፈልገው ከወር በፊት አስታውቆየነበረ ሲሆን ከዚህ ውስጥ እስካሁን የተገኘው 6.5 ከመቶው ብቻ ነው።