በኢትዮጵያ የንባብ ባህልን ለማሳደግ የሰሩት ጄን ከርትዝ ዓለም አቀፍ ተሸላሚ ሆኑ
Your browser doesn’t support HTML5
በኢትዮጵያ በርካታ መጽሃፍት ቤቶችን የገነባው እና የንባብን ባህል ለመሳደግ እየጣረ የሚገኘው ኢትዮጵያ ሪድስ አጋር መስራች ጄን ከርትዝ ዓለም አቀፉ ለወጣቶች የተጻፉ መጽሃፍት ቦርድ (IBBY) ያዘጋጀው ሽልማት አሸናፊ መሆናቸው ከሰሞኑ ይፋ ተደርጓል።የኢትዮጵያ ትዝታቸውን ጨምረው ከ40 በላይ የህጻናት መጽሀፍቶችን ያሳተሙት ጄን የላቀ ንባብ ባህልን በማጎልበት ረገድ ላበረከቱት፣ ዓመታትን ለተሻገረ አስተዋጽኦቸው ሽልማቱ እንደተሰጣቸው ታውቋል።