አጭር ቆይታ ፦ከቀድሞዋ የወጣት አፍሪካዊያን የአመራር መርሀ-ግብር(YALI) ተሳታፊ ራህዋ ገ/መስቀል ጋር

Your browser doesn’t support HTML5

በያመቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከመላ አፍሪካ የተመረጡ ወጣቶች በዩናይትድ ስቴትስ በሚገኙ የትምህርት ተቋማት በተለያዩ ዘርፎች የአጭር ጊዜ ትምህርት እና ስልጠና ይወስዳሉ ።ወደ ሀገራቸው ተመልሰው የተማሩትን እንዲተገብሩም ይበረታታሉ። የማንዴላ ዋሺንግተን ፌሎሺፕ በተባለው በዚህ መርሀ ግብር ተሳታፊ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ፣ ወደ ሀገር ቤት ከተመለሱ በኃላ በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ መጠየቅ ከጀመርን ቆየት ብለናል ። ለዛሬ ወደ አንደኛው ተሳታፊ ራህዋ ገ/መስቀል ስልክ መተናል ።