ሩሲያውያን እና ዩክሬናውያን በቨርጂኒያ አብረው እያመለኩ ነው

  • ቪኦኤ ዜና

የዩክሬን ተፈናቃዮች

ዘወትር እሁድ፣ በርካታ ዩክሬናውያንና ሩሲያውያን ክርስቲያን አማኞች፣ ቨርጂኒያ ውስጥ፣ ማውንት ክሮፎርድ ወደ ሚገኘው፣ የመጀመሪያው የሩሲያውያን ባፕቲስት ቤተከርስቲያን ለጸሎት ይሰባሰባሉ፡፡አማኞቹ ሩሲያ በዩክሬን ላይ በማካሄድ ላይ የምትገኘውን ወረራ የሚያወግዙ ቢሆንም፣ አንድ ባደረጋቸው ነገር ላይ ያተኮሩ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡

ሩሲያ ዩክሬንን ወረራ ከተፈጸመበት በሺዎች ኬሎ ሜትር ርቀት ላይ በቨርጂኒያ የገጠር ክፍል የተመሰረተው ይህ ቤተክስቲያን ከተገነባ 25 ዓመት ሆነው፡፡ ሰንበት በመጣ ቁጥር ሩሲያውያንና ዩክሬናውያን በዚህች ስፍራ ይሰበሰባሉ፡፡

በመጀመሪያው የሩሲያ ባብቲስት ቤተክርስቲያን ውስጥ አገልጋይ የሆኑት ዩክሬናዊው ያሪ ሱስሌቭ እንዲህ ይላሉ

“እግዚአብሄርን ለማምለክ ነው የመጣነው፡፡ በዩክሬን ያለው ግጭት በብዙ ያሳዝነናል ምክንያቱም ሁልጊዜም ራሳችንን እንደ ወንድማማችና እህትማማች የምቆንጠር ነን፡፡ አሁን በሩሲያና በዩክሬን መካከል እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ እያሳዘነን ነው፡፡”

አማኞቹ እዚህ ቨርጂኒያ ማውንት ክሮፎርድ በሚገኘው፣ የሩሲያ ባብቲስት ቤተከርስቲያን ውስጥ ጦርነቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲያበቃ ይጸልያሉ፡፡ ጦርነቱን የሚቃወሙ መሆኑንም ይናገራሉ፡፡

ከአማኞቿ አንዷ የሆኑት ሩሲያዊት ናሪና ድሮኖቭ እንዲህ ብለዋል

“ይህን ጦርነት በርግጥ የሚፈልጉ ሰዎች አሉ፡፡ አብዛኛው ህዝብ ግን አይፈልገውም፡፡ ይህ ጦርነት የሚያስፈልግ አይመስለኝም፡፡ ልዩነቶቻችንን ልንፈታባቸው የምንችላቸው ብዙ መንገዶች አሉ፡፡ ይሁን እንጂ ጦርነቱን የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉና እነዚያም ሰዎች ሥልጣን ያሉ በመሆናቸው ጦርነቱ የማይቀር ሆኗል፡፡”

Your browser doesn’t support HTML5

ዩክሬናውያንና ሩሲያውያን ክርስቲያን አማኞች በአንድ ላይ በመፀለይ ላይ ናቸው

ወዴ ቤተክርስቲያን የሚመጡት እነኝህ አማኞች በዚች ስፍራ ትኩረታቸውን ማድረግ የሚፈልጉት አንድ በሚያደርጋቸውና የጋራቸው በሆኑት ባህላዊ እሴቶቻቸው ላይ ነው፡፡ ጦርነቱ የተደባለቀ ማንነትና ቤተሰብ ባላቸው ሰዎች ላይ የበለጠ ጉዳት ማስከተሉን ይገልጻሉ፡፡ ዩክሬናዊቷ አማኝ ቫያሽስላቭ ሸንሶን እንዲህ ይገልጹታል

“እናቴ ሩሲያዊት ናት፡፡ የተወለድኩት ዩክሬን ሲሆን ያገባሁት ቤላሩሲያዊት ነው፡፡ ስለዚህ እኔ በግሌ የሶስት አገሮች ድብልቅ ነኝ፡፡ ይህ በመሆኑም እኔ ሩሲያውያንን ስወጋ፣ ወይም ሩሲያውያንም ከዩክሬናውያን ጋር ሲዋጉ አይታየኝም፡፡ በርግጥ ይህን የፈጠረው ፑቲን ነው፡፡ ስለዚህ ለኔ እንደ አማኝ ጠንክረን መቆም አለብን ብዬ አስባለሁ፡፡ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸውና ሰላም መፍጠር የሚጥሩ ሰዎችን መርዳታ አለብን፡፡”

ከሩሲያ የመጡ ሩሲያዊት አማኝ አንዘሊካ ዩርሼንኮም በበኩላቸው እንዲህ ብለዋል

“የመለያያት እድሉ ያለ ይመስለኛል፡፡ ይሁን እንጂ ግን ከተለያየ አካባቢ የመጣንም ሰዎች ብንሆን መረዳዳት አለብን ብዬ አስባለሁ፡፡ እኔ በበኩሌ አንዳችንም ቢሆን ይህን ጦርነት እንፈልገዋለን ብዬ አላስብም፡፡ ስለዚህ ከየትም እንምጣ፣ ከየትም እንሁን፣ እጅ ለእጅ ተያይዘን መደጋገፍ ይኖርብናል፡፡”

ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ዩክሬን ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል፣ ከ2 ሚሊዮን ግማሽ ተኩል በላይ የሚሆኑት ደግሞ ወደ ጎበረቤቱ የአውሮፓ አገሮች ሸሽተዋል፡፡

(ዘገባው የያያ ብራዚኒ ነው፡፡)