የናይጄሪያ ወጣቶችና የፖለቲካ ተሳትፏቸው

Your browser doesn’t support HTML5

ናይጄሪያውያን የሚቀጥለው ዓመት ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ለመሄድ እየተዘጋጁ ነው። ሆኖም ለአስርት ዓመታት ሥልጣን ላይ የቆዩትን የቀደመው ትውልድ አባላትን ከሥልጣን ማስወገድ የሚችሉ ወጣቶች በእጩነት ቀርበው እንዲፎካከሩ የወጣት ቡድኖች ጥሪ እያቀረቡና እየገፋፉ ነው። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2020 የፖሊሶችን ጭካኔና የከፉ የተባሉ መሪዎችን ለማወስወገድ የነበረው የወጣቶች እንቅስቃሴም በአዲስ አስተሳሰብ ተመልሶ እየመጣ ነው። ግን ደግሞ የናይጄሪያ ወጣቶች ወደ ፖለቲካው ዓለም መግባት ብዙ ፈተና የተጋረጠበት መሆኑ ከወዲሁ እየታያቸው መሆኑኑ ይናገራሉ፡፡ /ዘገባው ቲሞቲ ኦቪዙ ከአቡጃ ያጠናቀረው ነው።