የራሺያና የዩክሬን ጦርነት በኢትዮጵያና ኤርትራ ላይ የሚያሳድረው ተጽኖ ምንድነው?
Your browser doesn’t support HTML5
በራሽያ እና በዩክሬን መካከል የተጀመረው ጦርነት እና በራሽያ እና በምዕራብ ሀገራት መካከል እየጨመረ የመጣው መካረር ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ ሀገራትን አጣብቂኝ ውስጥ ሊከታቸው እንደሚችል የፖለቲካ ተንታኞች ስጋታቸውን ገልፀዋል። አስተያየታቸውን ያካፈሉን የዓለም አቀፍ ግንኙነት መምሕሩ ፕሮፌሰር ጌታቸው መታፈሪያ ፣ በዋሽንግተን ዲሲ የሕግ ባለሞያ እና የግጭት ተንታኝ አቶ አለማየሁ ፈንታ ወልደማሪያምና የፖለቲካ ተንታኝ አቶ አብዱርኸማን ሰይድ ናቸው።