ትምኒት ገብሩ በአዲስ የሰው ሰራሽ ልኅቀት ምርምር ተቋም

Your browser doesn’t support HTML5

ከአንድ ዓመት በፊት “ጉግል” ከተሰኘው ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ የተባረረችው ትምኒት ገብሩ ለጥቁሮች እና ሴቶች ፍትሐዊ ቴክኖሎጂ የሚታገል የሰው ሰራሽ ልኅቀት የምርምር ተቋም መስርታለች። ተቋሙ እንደ ፎርድ እና ማካርተር ፋውንዴሽን ከመሳሰሉ ትልልቅ ተቋማት የ3.7 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ የተደረገለት ሲሆን ጥቁር ሴቶችን ጨምሮ በቴክኖሎጂ መገለል የሚደርስባቸው የማኅበረሰብ አካላት ዙሪያ በገለልተኝነት እንደሚሠራ ትምኒት ለአሜሪካ ድምፅ ተናግራለች።