ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ላይ የደረሰው ጥቃት አስከፊ መሆኑ ተመድ ገለፀ

Your browser doesn’t support HTML5

ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ላይ የደረሰው ጥቃት አስከፊ መሆኑ ተመድ ገለፀ

ከአምስት ቀናት የአዲስ አበባ ቆይታቸው ወደ ኒው ዮርክ የተመለሱት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና ሞሃመድ በግጭት አካባቢ ባሉ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ላይ የደረሰው የጾታዊ ጥቃት፣ ጉዳትና በደል አስከፊ መሆኑን ተናግረዋል።

“በዚህ ጦርነት የሚሳተፉ በሙሉ አሸናፊ አይደሉም” ብለዋል። ም/ዋና ጸሐፊዋ አያይዘው “የጦርነቱ ተሳታፊዎች ኢትዮጵያዊ መፍትሄ ለማምጣት ተነሳሽነት እንዳላቸው አስታውቀውናል” ብለዋል፡፡