የቦረና ዞንና የሶማሌ ድርቅ አሳሳቢ እየሆነ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

በኦሮምያ ክልል ቦረና ዞን ውስጥ መስከረም ውስጥ የተጠበቀው ዝናብ ባለመጣሉና ለስድስት ተከታታይ ወራት እርጥበት በመጥፋቱ ምክንያት የተከሰተው ድርቅ ቁጥራቸው የበዛ ከብቶችን መጨረሱን የክልሉ ግብርና ፅህፈት ቤት የእንስሣት ኃብት ልማት ቢሮ አስታውቋል። የቢሮው አስተባባሪ ዶክተር ቃሲም ጉዮ እስካሁን ከአራት ቢሊዮንብር በላይ የሚያወጡ ከብቶች መሞታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና የኦሮምያ ፕሬዚዳንት አቶ ሺመልስ አብዲሳ ዛሬ ቦረና ተገኝተው የድርቁን ሁኔታና ያስከተለውን ጉዳይ ተመልክተዋል።