በሁቲ አማጺያን የተያዙት ኢትዮጵያዊ መርከበኛ ቤተሰቦች የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ድጋፍ ጠየቁ
Your browser doesn’t support HTML5
ከቀናት በፊት በየመን አማጺያኑ እጅ ከወደቁት መርከበኞች መካከል አንዱ እንደሆኑ የተነገረላቸው ኢትዮጵያዊ ቤተሰቦች ፣ የደህነነት ሁኔታቸውን ለማወቅ መቸገራቸውን ለአሜሪካ ድምጽ ተናገሩ።
“ሩዋቢ” በተሰኘው መርከብ ላይ በመሃንዲስነት እያገለገሉ የነበሩት አቶ አየናቸው መኮነን ነጻነታቸውን ዳግም ያገኙ የኢትዮጵያ መንግስት እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲያግዟቸው ቤተሰቦቻቸው ጠይቀዋል ።