ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ጅምር

Your browser doesn’t support HTML5

በጦርነቱ ምክኒያት ከተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ተፈናቅለው ደብረብርሃን ከተማና በሌሎች የሰሜን ሸዋ ዞን አካባቢዎች ተጠልለው የነበሩ ተፈናቃዮች ወደ አካባቢያቸው መመለስ ጀምረዋል። ተፈናቃዮቹ በደብረብርሃን በቆዩባቸው ጊዜያት የነበራቸውን ገንዘብ ከመጨረስ አልፎ ንብረቶቻቸው ስለመወደመባቸው ወደ ቀያያቸው ሲመለሱም የሚደረግላቸው ድጋፍ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
ተፈናቃዮቹ የእርዳታ አቅርቦት እንዳይቋረጥባቸው እየተሠራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የሰሜን ሸዋ ዞንምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ወልደ አማኑኤል ናቸው፡፡