ወጣቱ የቴክኖሎጂ ፈጣሪ በተደረገለት ድጋፍ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መማር ጀመረ

Your browser doesn’t support HTML5

የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለ ስማርት ሀውስ ወይም የውጪውን ሁኔታ በማስተዋል እራሱን የሚቆጣጠር ቤት እና የስልክ አጠቃቀምን የሚያቀል መተግበሪያ በመስራት ሀገር አቀፍ ሽልማቶችን ያገኘው ወጣት ናትናኤል ታምሩ ከአራት ወር በፊት የፕሮግራማችን እንግዳ ነበር። በዚህ የፈጠራ ስራውና የትምህርት ብቃቱ ካሊፎርኒያ የሚገኘው ሚነርቫ ዩንቨርስቲ ነፃ የትምህርት እድል ቢሰጠውም ለጉዞ የሚያፈልጉትን ወጪዎች ለመሸፈን አለመቻሉን ነግሮን የነበረው ናትናኤል በፕሮግራማችን ላይ ከቀረበ በኃላ በተደረገለት ድጋፍ ወደ ሳንፍራንሲስኮ ከተማ አቅንቶ በሰው ሰራሽ ልህቀት (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) የመጀመሪያ አመት ትምህርቱን መከታተል ጀምሯል።