ኦሚክሮን በብዙ ሃገሮች እየታየ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

ለመጀመሪያ ጊዜ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የታየው አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ኦሚክሮን በተለያዩ የዓለም አካባቢዎች እየታየ ነው። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዋና የጤና አማካሪ አንተኒ ፋውቺ ኦሚክሮን ከሌሎቹ የኮሮናቫይረስ ዝርያዎች የበለጠ ተላላፊ መሆኑን ቢገልፁም የጤና ባለሙያዎች ግን “የበለጠ ህመም ያስከትል ይሆን ወይ?” ለሚለው እርግጠኛ አይደሉም።