ፒቪኤች የሃዋሳ ሥራውን አቆመ

Your browser doesn’t support HTML5

በሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለዓመታት ሲሠራ የቆየው «ፒቪኤች» የሚባል የአሜሪካ ኩባንያ ሥራ ማቆሙን አስታውቋል። ሥራ በማቆሙ ማዘናቸውን የገለፁት የፒቪኤች ሠራተኞች ካሣ እንደሚፈላቸው ቢነገራቸውም እስከ አሁን ግን እንዳልተከፈላቸው አመልክተዋል። ለችግር መጋለጭ መጀመራቸውን ጠቁመው የፓርኩ አስተዳደር በገባው ቃል መሠረት ፈጥኖ ወደ ሥራ እንዲያሠማራቸው ጠይቀዋል።