“ ከእኔ ይልቅ ሽልማቱ የሚገባው (ለጦርነቱ ሰለባዎች ) ፣ ለእነሱ ነው ”-የምስል ዘጋቢ ሶለን ገመቹ

Your browser doesn’t support HTML5

የ"ማይካድራ ጭፍጨፋን " ጨምሮ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የደረሱ አሰቃቂ ትዕይንቶች በምስል ከሰነዱ ጋዜጠኞች መካከል አንዱ የሆነው ሶለን ገመቹ ከሰሞኑ የ ሮሪ ፔክ ሽልማትን አሸንፏል። በስራቸው የላቀ ብቃት ላሳዩ ፍሪላንስ ጋዜጠኞች የሚሰጠውን ሽልማት የተቀበለው ሶለን ከስራው ጋር የተገናኙ ትውስታዎቹን እና የሽልማቱን ፋይዳ ለሀብታሙ ስዩም አጋርቶታል ።