መንግሥት “ሸኔ” ባላቸው ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

በኦሮምያ ምዕራብ ሸዋና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች ውስጥ የሚንቀሳቀሱ በርካታ የሸኔ በሚላቸው ታጣቂዎች ላይ መንግሥት እርምጃ መውሰዱን የፌደራል መንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ አገልግሎት አስታውቋል። ያሉት እርምጃ የተወሰደው ባለፉት ሁለት ሣምንታት ውስጥ መሆኑን የአገልግሎቱ ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ ጠቅሰው የተገደሉና የተማረኩ ታጣቂዎች መኖራቸውን ገልፀዋል።