ደቡብ ክልል የእንቅስቃሴና የሰዓት እላፊ ገደቦችን አነሳ

Your browser doesn’t support HTML5

የደቡብ ክልል አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ ጥሏቸው የነበረውን የእንቅስቃሴና የሰዓት እላፊ ገደቦችን ማንሳቱን አስታውቋል። ገደቦቹ የተነሱት የክልሉ ህዝብ የአከባቢውን ሰላም እና ህግ በማስከበር ሂደት ውስጥ በንቃት መሳተፍ በመጀመሩ እና ገደቡ በኢኮኖሚያ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ ሲባል መሆኑን የክልሉ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዓለማየሁ ባውዲ ለቪኦኤ ገልፀዋል።