የደቡብ ክልል ቀጣይ ዕጣ ፋንታ

Your browser doesn’t support HTML5

በደቡብ ክልል እየተመሰረቱ የሚገኙ ክልሎች የሕዝብ ችግር የሚፈቱ እንጂ ተጨማሪ ፈተና ይዘው የሚመጡ መሆን የለባቸውም ሲሉ ምሁራን ተናገሩ። “ክልሉን ወደ ተለያዩ ክልሎች መከፋፈሉ ሕዝቡ የራሱን ዕድል በራሱ ጊዜ እንዲወስን እድል ይሰጠዋል” ያሉት በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ መምሕሩ ዶ/ር ንጉስ በላይ ናቸው።
የዓለም አቀፍ ግንኙነትና የፖለቲካ ሳይንስ ምሑሩ አቶ ዳያሞ ዳሌ፤ “ክልሉ እየተበታተነ ያለው የክልሉ ሕዝብ ጥያቄ ስላልተመለሰ ነው” ብለዋል። “የክልሉ የበጎ ጎን ዕጣ ፈንታም የሚወሰነውም በኢትዮጵያ አንድነት ነው” ሲሉ ተናግረዋል።