የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለአደጋ ካጋለጡ ኃይሎች ድርድር እንደማይደረግ አምባሳደር ዲና ተናገሩ

Your browser doesn’t support HTML5

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሠራተኞች የታሰሩት የኢትዮጵያን ሕግ በመጣስ ተጠርጥረው እንደሆነ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ቃል አቀባይ ተናገሩ።
ተመድ በበኩሉ ሠራተኞቹን ለማስፈታት ጥረት እያደረገ እንደሆነ ገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ሁልጌዜም ለሰላም የቆመ ቢሆንም የሃገር ሉአላዊነትን ለአደጋ ካጋለጡ ኃይሎች ጋር ለመደራደር እንደማይቻል ቃል አቀባዩ አምባሳደር ዲና ሙፍህ በዛሬው መግለጫቸው ላይ ተናግረዋል።