ህወሃት ትጥቁን ፈትቶ ወደ ትግራይ ካልተመለሰ ድርድር እንደማይኖር የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

ህወሃት ከአማራና ከአፋር ክልል ሙሉ ለሙሉ ካልወጣና እያካሄደ ያለውን ሁከት እና ጥቃት ሙሉ ለሙሉ ካላቆመ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ምንም ዓይነት ድርድር ሊካሄድ እንደማይችል ሁለት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ወቅታዊ ጉዳዮች በማስመልከት ዛሬ ለአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርና ለውጭ መገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ፍትህ ሚኒስቴር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ቃል አቀባይ ቢልለኔ ስዩም ወቅታዊ ጉዳዮች በማስመልከት ዛሬ ለአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርና ለዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች በኢንተርኔት ላይ በተደረገ ውይይት በሰጡት መግለጫ፤ ህወሃት በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች ጥቃት ለማድረስ እያሴረ መሆኑ ተጨባጭ የደህንነት መረጃ እንደደረሳቸው ገልፀዋል።