በሰሜን ሸዋ የሚገኙ ተፈናቃዮች በቀውስ ውስጥ እንደሚገኙ ገለፁ

Your browser doesn’t support HTML5

ከደሴና ኮምቦልቻ ከተሞች እንዲሁም በዙሪያው ካሉ አካባቢዎች ተፈናቅለው ወደ ሰሜን ሸዋ የገቡ የኅብረተስብ ክፍሎች“በአሳሳቢ ሰብአዊ ቀውስ ውስጥ እንገኛለን” ሲሉ ገለጹ፡፡ተፈናቃዮቹ የመንግሥትንና የበጎ አድራጊዎችን ድጋፍ ጠይቀዋል።የአማራ ከልል አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትናና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን በሕግ ማስከበር፤በማንንትና በግጭት ሲሉ በገለጿቸው ምክንያቶች ከ2ሚሊዮን በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎች በክልሉ ውስጥ ሳይፈናቀሉ እንደማይቀር አስታውቋል፡፡