የሐረሪ ክልል መንግሥት ምስረታና የቀረበው ቅሬታ

Your browser doesn’t support HTML5

የሐረሪ ክልል መንግሥት ምሥረታ ባለፈው ዓርብ ተካሂዷል። የክልሉ ምክር ቤት ጉባዔ ለርዕሰ መስተዳደርነት የቀረበለትን ዕጩ ተቀብሎ አፅድቋል።
በአሿሿሙ ሂደት ላይ የአቋም ልዩነት የነበራቸው እንደራሴዎች “ወደ አዳራሽ አንገባም” በማለታቸው “ምልዓተ ጉባዔ አልተሟላም” ተብሎ ስብሰባው ተበትኖ የነበረ ቢሆንም ስብሰባው ከሰዓት በኋላ ተጠርቶ ምርጫው ተካሂዷል።
አዲሱ የክልሉ ካቢኔ ሌሎች ክልሎች እንዳደረጉት የተፎካካሪ ፓርቲዎች አባላትን አላካተተም።