አቶ እስክንድር ነጋ ማረሚያ ቤት ውስጥ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ፓርቲያቸው አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

አቶ እስክንድር ተፈጽሞባቸዋል በተባለው ድብደባ ምክንያት ዛሬ በነበራቸው ቀጠሮ ችሎት እንዳልተገኙ የፓርቲው ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸዋል፡፡
ድብደባው የተፈጸመባቸው ከዚህ ቀደምም ያሰጓቸው ስለነበር ወደ ሌላ ማረሚያ ቤት ከተወሰዱ በኋላ በድጋሚ ወደ ቂሊንጦ በተመለሱ ግለሰቦች መሆኑን የገለጹት ደግሞ ጠበቃቸው ሄኖክ አክሊሉ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ፣ ስለጉዳዩ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት አስተያየት ክስተቱ በግለሰቦች መካከል የተፈጠረ አለመግባባት እንጂ ሆነ ተብሎ አቶ እስክንድርን ለማጥቃት ታስቦ የተደረገ አይደለም ብለዋል፡፡