በመቀሌ ከተማና አቅራቢያው ተፈፀመ በተባለ የአየር ጥቃት ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ
Your browser doesn’t support HTML5
የኢትዮጵያ መንግሥት ድርጊቱን አስተባብሏል
በመቀሌ ከተማና በአቅራቢያው ባለ ገጠር ቀበሌ ተፈጽሟል ባሉት የአውሮፕላን ጥቃት የሰው ሕይወት ማለፉና ነዋሪዎች መቁሰላቸውን፤ በጥቃቱ የተጎዳ ነዋሪና የሕክምና ባለሞያ ገለፁ።በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ የተባለው ጥቃት ማስተባበላቸውን እና “የኢትዮጵያ መንግስት የገዛ ከተማዎን ለምን ያጠቃል? መቀሌ የኢትዮጵያ ከተማ ናት ። ’’ ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።