ከራያ ቆቦ ዋጃ አካባቢ የተፈናቅሉ ደሴ ከተማ መግባታቸውን ገለፁ

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት የፈረጀውና እራሱን የትግራይ ኃይል ብሎ በሚጠራው በህወሓት ታጣቂ ቡድን ቁጥጥር ሥር መሆኑ ከሚነገረው ከራያ ቆቦ ዋጃ አካባቢ ከ1 ሺሕ በላይ ነዋሪዎች ተፈናቅለው ደሴ ከተማ መግባታቸውን ገለፁ።
አብዛኛውን ቁጥር የሚይዙት ወጣቶች መሆናቸው የሚናገሩት ተፈናቃዮቹ፤ በመኖሪያ መንደራቸው ተከሰተ ያሉትን ጫና ተቋቁሞ ለመቆየት ያደረጉት ጥረት ስላልተሳካላቸው መፈናቀላቸውን ተናግረዋል።