ቁጫ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አባላቱ ለእስር መዳረጋቸውን ገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

ቁጫ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አባላቱ ለእስር መዳረጋቸውን ገለጸ

የቁጫ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በደቡብ ክልል ጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ አባላቱ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ያለ አግባብ እየታሰሩ መሆኑን በመግለፅ አቤቱታ አሰማ። ከ150 በላይ አባላቱ በእስር ላይ እንደሚገኙም አስታውቋል።

የጋሞ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ግለሰቦቹ የታሰሩት በወንጀል ተጠርጥረው ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባኤ በበኩሉ ስለ አባላቱ እስርና ተፈፅሞባቸዋል ስላለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት መረጃው እንዳለው ገልፆ፤ የሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን ማጣራት አድርገው ፍትህ እንዲያሰፍኑ ጠይቋል።