የኦሞ ወንዝ ሞልቶ ከ62ሺህ በላይ ነዋሪዎች ተፈናቀሉ

Your browser doesn’t support HTML5

በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን በዳሰነች ወረዳ የኦሞ ወንዝ ሞልቶ ከ62ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸው እና ለችግር መጋለጣቸውን የአካባቢው ባለ ሥልጣናት ይፋ አደረጉ።
የደቡብ ኦሞዞን አስተዳደር በበኩሉ “በየዓመቱ ይከሰታል ያለውን የኦሞ ወንዝ የመጥለቅለቅ አደጋ በዘላቂነት ለማስቀረት የክልል እና የፌዴራል መንግሥት በጥናት ላይ የተመሰረተ እርምጃ መውሰድ አለባቸው” ሲል አሳስቧል።