የጭና ነዋሪዎች “የህወሓት ታጣቂዎች ፈፅመውብናል” ካሉት ጥቃት እንዳመለጡ ተናገሩ

Your browser doesn’t support HTML5

በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ጭና ተክለ ኃይማኖት ቀበሌ ነዋሪ የሆኑና “የህወሓት ታጣቂዎች ፈፅመውብናል” ካሉት ጥቃት እንዳመለጡ የሚናገሩ ነዋሪዎች የህወሓትን ምላሽ እንደማይቀበሉት ተናገሩ። የህወሓት ታጣቂዎች ከነሀሴ 24 ሌሊት አንስቶ ለአምስት ቀናት መቆየታቸውን እና ከዚያም ጥቃቱን እንደፈፀሙባቸው የትኛውም ገለልተኛ የሆነ አካል ወደ መንደራቸው ሄዶ ማጣራት የሚችለው ሃቅ ነው ብለዋል።