የተፈናቃዮች ቁጥር ማሻቀቡን መንግሥት አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

መንግሥት በአሸባሪነት የፈረጀውና ራሱን የትግራይ ወታደራዊ ኃይል እያለ የሚጠራው አካል ወደ አማራ ክልል ዘልቆ መግባቱን ተከትሎ ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከግማሽ ሚሊዮን መብለጡን የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትናና ድጋፍ የሚፈልጉ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ወታደራዊ ወረራ ተፈጽሞባቸዋል በተባለባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ከ700ሺሕ በላይ የሴፍቲኔት ተጠቃሚ አርሶ አደሮችን አፋጣኝ ርዳታ ለማድረስ አለመቻሉንም ኮሚሽኑ ጨምሮ ገልጿል።