የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት በሃዋሳ

Your browser doesn’t support HTML5

የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች በዋጋ ንረት ሳቢያ በተከሰተው የኑሮ ውድነት መማረራቸውን ገለፁ። የከተማው አስተዳደር ሕግ ተላልፈው በተገኙ፥ ያልተገባ ዋጋ በጨመሩ እና ዜጎችን በማስጨነቅ ላይ ያሉ ነጋዴዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስታውቋል።
በዋጋ ንረት እና በኑሮ ውድነት ላይ የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ከከተማው ነዋሪዎች እና ነጋዴው ማኅብረሰብ ጋር ውይይት ያካሄደ ሲሆን የከተማውን ሕዝብ በኑሮ ውድነት መማረሩ ተገልጿል።
የዋጋ ንረት በኅብረተሰቡ ላይ የሚያሳድረውን ጫና ለመቀነስ ሲባል ቀረጥ፥ ታክስ እና ተጨማሪ እሴት ታክስዎችን ከተለያዩ ምርቶች ላይ ማንሳቱን የንግድ ሚኒስቴር አስታውቋል።